የ’ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰልፍ በሎስ አንጀለስ ከተማ ተካሄደ

ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ) የ’ኤች አር 6600’ እና የ’ኤስ 3199′ ረቂቅ ሕጎች የሚቃወም ሰልፍ በካሊፎርኒያ ግዛት ሎስ አንጀለስ ከተማ ተካሄደ።

ሰልፉ የ’ኤችአር 6600′ ረቂቅ ሕግን በተባባሪነት ያዘጋጁት የካሊፎርኒያ የኮንግረስ አባል ብራድ ሼርማን ቢሮ ፊት ለፊት ነው የተካሄደው፡፡

በሰለፉ ላይ ኢትዮጵያዊያን፣ ኤርትራዊያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች ’ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ 3199’ ረቂቅ ሕጎች እንደሚቃወሙትና ሕጎቹ ኢትዮጵያን እንዲሁም በኢትዮጵያና አሜሪካ መካከል ያለውን ግንኙነት የሚጎዳ በመሆኑ ውድቅ እንዲደረግ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

“ማዕቀብ ይገድላል ይጎዳል”፣ “ረቂቅ ሕጎቹ የምስራቅ አፍሪካን ሰላምና መረጋጋት አደጋ ላይ የሚጥሉ ናቸው” እና ሕጎቹ በየትኛውም አይነት ሁኔታ የኢትዮጵያንና አሜሪካን ጥቅምና ፍላጎት አያስጠብቁም” የሚሉ መፈክሮች በሰልፉ ላይ መስተጋባታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ኤች አር 6600’ እና ‘ኤስ.3199’ ረቂቅ ሕጎችን የሚቃወም ሰላማዊ ሰልፍ ቀደም ብሎ በዋሺንግተን ዲሲ ዋይት ሃውስ ፊት ለፊት እንዲሁም ጣሊያን ሮም መካሄዱ የሚታወስ ነው።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW