የኤጀንሲ ሰራተኞች የ”ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ንቅናቄን መቀላቀል

መስከረም 14/2014 (ዋልታ) የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ሰራተኞች የ”ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ንቅናቄን ተቀላቀሉ።

ሰራተኞቹ የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ በሚል የተጀመረውን የ”ነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግስት” ንቅናቄን  በመቀላቀል ፊርማቸውን አኑረዋል።

አሸባሪው ሕወሓት እያደረሰ የሚገኘውን የሽብር ቡድኑን ድርጊት አይቶ ዝምታን የመረጠው ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በተለይ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና ለማሳደር የምታደርገውን እንቅስቃሴ እንደሚቃወሙም ተናግረዋል።

ኤጀንሲው ለመከላከያ ደም ከመለገስ ጀምሮ የተለያየ ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩት የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዳባ ኦርያ፣ ሀገራዊ ዘመቻዎች ላይ የምናደርገውን ተሳትፎ አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

በትዕግስት ዘላለም