የእሬቻ በዓል መስከረም 21 እና 22 እንደሚከበር ተገለጸ

የኦሮሞ አባ ገዳዎች

መስከረም 10/2015 (ዋልታ) 2015 ዓ.ም የእሬቻ በዓል መስከረም 21 ሆራ ፊንፊኔ፣ መስከረም 22 ደግሞ በቢሾፍቱ ሆራ ሃርሰዴ እንደሚከበር የኦሮሞ አባ ገዳዎች አስታወቁ፡፡

የኦሮሞ አባ ገዳዎች ሕብረት የኢሬቻ በዓል አከባበርን አስመልከተው በሰጡት መግለጫ የእሬቻ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የአባ ገዳዎች ሕብረት ሊቀመንበር አባ ገዳ ጂሎ ማን’ዶ የዘንድሮ የእሬቻ በዓል የኦሮሞን ህዝብ ባህል እና እሴት ተከትሎ እንዲከበር ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ አሳስበዋል።

የአባ ገዳዎች ህብረት ፀኃፊ እና የቱለማ አባገዳ ጎበና ሆላ የእሬቻ በዓል የቱሪዝም መስህብ ሆኖ እንዲቀጥል ለክብረ በዓሉ የሚመጡ ሰዎች የባህል አልባሳት እና መዋቢያ ጌጦችን በመልበስ እንዲያደምቁ ጥሪ ማስተላለፋቸውን ከኦቢኤን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW