የእስካሁኑ ጥፋት ይብቃ፤ ከአሁን በኋላ ችግሮቻችንን በምክክር እንፍታ – ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ

ሚያዝያ 4/2014 (ዋልታ) እስካሁን የጠፋው ጥፋት ይብቃ ከአሁን በኋላ ችግሮቻችንን በምክክርና በውይይት እንፍታ ሲሉ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ ገለፁ።

ተቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ዑመር ኢድሪስ እንደተናገሩት እስካሁን የጠፋው ጥፋት ይበቃል በማለት ፊትን ወደ ሰላም ማዞር ይገባል።

አገርን ለማስቀጠል የአገራዊ ምክክሩ ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ የጠቆሙት ፕሬዝዳንቱ ምክክሩ እኩልነት በሰፈነበት፤ በእውነትና በአንድነት መንገድ የሚከወን ከሆነ ለአገራችን አዎንታዊ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

መመካከርና መወያየት የቆየ የኢትዮጵያዊያን ትወፊት እንደሆነ ያወሱት ሃጂ ዑመር በመመካከርና በመወያየት ችግራችንን ልንፈታ ይገባል ሲሉም ተናግረዋል።

ተቀዳሚ ሙፍቲው አገራዊ ምክክሩ ወደታች ወርዶ ተፈፃሚ እንዲሆን እንዲሁም አገር ወደ ሰላማዊ ሁኔታዋ እንድትመለስ ከመንግሥትና ከኅብረተሰቡ ብዙ ይጠበቃል ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW