የእንስሳት መኖ ምርትን ከግብር ነፃ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

የእንስሳት መኖ ምርት

ጥቅምት 4/2015 (ዋልታ) የእንስሳት መኖ ምርትን ከግብር ነፃ ለማድረግ የሚያሥችል ስራ እየተሠራ መሆኑን ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በሚኒስቴሩ የመኖ ሃብት ልማት መሪ አሥፈፃሚ አርዓያ አብርሃም እንደገለፁት ከመኖ ምርት ጋር ተያይዞ በተለይም ደግሞ ከዋጋው አንፃር ያለውን ችግር ለማስተካከል አጠቃላይ የመኖ ግብይትን ከቀረጥ ነጻ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

ደንብ እየተዘጋጀለት የሚገኘው አሰራሩ ከቀጣዩ ኅዳር ወር ጀምሮ ወደ ሥራ ለማሥገባት ዝግጅቱን አጠናቋልም ነው ያሉት ኃላፊው።

ከዚህ በተጨማሪም አርሶ አደሩ እና በእንስሳት ማርባት እና አቅርቦት ስራ ላይ የተሠማሩ አካላት መኖን በአግባቡ እያመረቱ አቅርቦቱን አስተማማኝ ለማድረግ የመኖ ልማት ፕሮጀክት ተቀርፆ ስራ እየተሠራበት እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡

እንደኤፍቢሲ ዘገባ ሚኒስቴሩ የእንስሳት መኖ ምርትን ከግብር ነፃ ለማድረግ የወሰነው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሚገኘው የእንስሳት ተዋፅኦ ምርቶች ዋጋ ለተጠቃሚዎች ከፍተኛ ችግር መፍጠሩን በመገንዘብ ነው ብሏል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW