ሐምሌ 30/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ የክልሉን የትምህርት ጥራት ለማሳደግ የሚያስችለውን ስምምነት የተፈራረመ።
ቢሮው ስምምነቱን ከሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ህብረት ጋር ነው ተፈራረመው።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የክልሉን የትምህርት ተደራሽነት እና ጥራቱን ለማሳደግ ትኩረት ሰቶ እየሰራ ይገኛል። ለዚህ ደግሞ በ2013 ዓ.ም የበጀት ዓመት የተገነቡ 100 ኢፋ ቦሩ የሁለተኛ ደረጃ እና 7 ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤቶች ማሳያ ናቸው።
የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ተጠናቆ ወደ ስራ በሚገቡበት ወቅት የሚሰጡት ትምህርት ጥራቱ ተጠብቆ ሀገር ተረካቢው ትውልድ ጥራት ያለውን የትምህርት አገልግሎት ማግኘት አለበት።
ይህን ለማሳካት ያስችለውም ዘንድ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ከሚኒስቴርጨመስርያ ቤቱና የዩኒቨርሲቲዎች እና ኮሌጆች ህብረት ጋር የጋራ ስራ ስምምነት አድርጓል።
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ቶላ በሪሶ (ደ/ር) የትምህርት ጥራቱ እንደ ሀገር ችግር ውስጥ መኖሩን አንስተውጰይህን ችግር ለመፍታት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እና ታች መካከል ያለውን ክፍተት መሞላት አለበት ነው ያሉት።
ዩኒቨርሲቲዎች በያሉበት አከባቢውን የመቀየር ሀላፊነት አለባቸው ያሉት ሀላፊው ይህንጰመሠረት በማድረግ ለትምህርቱ ዘረፍ ትኩረት ሰተውት በሚችሉት መደገፍ አለባቸው ነው ያሉት።
አሁን የክልሉ መንግስት ባስገነባቸው ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ሁለት ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ትምህርት ቤት እገዛ ያደርጋሉ። እገዛው ከሰውጰኋይል አንስቶ እስከሚያስፈልጉ የትምህርት ቁሳቁሶች ናቸው።
የሳይንስ እና ከፍተኛ የትምህርት ሚንስትር ዴታ ሳሙኤል ክፍሉ (ዶ/ር) ክልሉ በትምህርቱ ዘርፍ እያከናወነ ያለውን ክራ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሶስተኛ ሀላፊነታቸው በሆነው ማህራዊ አገልግሎቶት ለትምህርት ዘርፊ ድጋፍ በማድረግ ሀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ነው ያሉት።
26 አባላት ያሉት የኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ማህበር ሊቀመንበር ለሚ ጉታ (ዶ/ር) የትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ ዩኒቨርሲቲዎች ትኩረት ሰተው መስራት እንዳለባቸውጰአሳስበዋል።
(በሚልኪያስ አዱኛ)