የኦሮሚያ ክልል ለሱማሌ ክልል አርብቶአደሮች ከ3 ሚሊየን ብር በላይ ግምት ያለውን የእንስሳት መኖ ድጋፍ አደረገ

መጋቢት 13/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልል ለሱማሌ ክልል አርብቶ አደሮች 3.1 ሚሊየን ብር ግምት ያለው የእንስሳት መኖ ድጋፍ አድርጓል፡፡
የሱማሌ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ም/ኃላፊ አቶ አብዱልፈታህ መሐመድ ድጋፉን ሲረከቡ፣ የኦሮሚያ ክልል ድጋፉን ያደረገው በወሳኝ ወቅት በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግስትን በመወከል ድጋፉን ወደ ሱማሌ ክልል የወሰዱት አቶ ሽብሩ ሆርዶፋ፣ የኦሮሚያ ክልል መንግስት የሱማሌ ክልል አርብቶ አደሮች ችግር ችግሬ ነው በማለት ካለው ውስን ሀብት ድጋፍ እንዳደረገ መግለጻቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡