የኦሮሚያ ክልል ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ

ኅዳር 14/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት አዲስ ለተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሕዝቦች እና ወደ አመራርነት ለመጡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

ኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን በጠንካራ መሰረት ላይ ለመጣል በምታደርገው ጥረት ውስጥ እናንተ ሰላማዊ በሆነ መንገድ የክልልነት ጥያቄያችሁ አወንታዊ ምላሽ እንዲያገኝ ያደረጋችሁት ጥረት እንደ መሰረት ድንጋይ የሚታይ እና እንደ ማሳያም የሚነሳ እንደሚሆን ክልላችን በጽኑ ያምናል ብሏል በመልዕክቱ፡፡

በቀጣይም የኦሮሚያ ክልል መንግሥትና መላው የክልሉ ሕዝብ ከአዲሱ ክልል ጎን እንደሚቆምም አረጋግጧል።

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
https://www.facebook.com/waltainfo
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
https://bit.ly/3vmjIZR
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/WALTATVEth
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ

አብራችሁን ስለሆናችሁ ደስተኞች ነን!