የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ምስረታ

የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ምስረታ

መስከረም 15/2014 (ዋልታ) አዲሱን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የሚመሰርተው የጨፌ ኦሮሚያ ጉባኤ እየተካሄደ ነው።

ምልዓተ ጉባኤው በአባ ገዳዎች ምርቃት መክፈቻውን አድርጎ በመካሄድ ላይ ነው።

በዚህም አዲሱ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት ዛሬ የሚመሰረት ይሆናል።

በ6ኛው አገራዊ ምርጫ ለጨፌ ኦሮሚያ ምክር ቤት አባልነት የተመረጡ አባላት በመጀመሪያ ጉባኤያቸው ክልሉን ለ5 ዓመት የሚመራ አካልን ያደራጃሉ።

አዲሱ ጨፌ በመጀመሪያ ጉባኤው አዲሱን የክልሉን ርዕሰ መስተዳድር ጨምሮ አዲስ የካቢኔ አባላት እንደሚሰይምም ይጠበቃል።

በሰኔ 14ቱ ምርጫ የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲ ማሸነፉ ይታወሳል።

በነሞምሳ አድማሱ