የኦሮሚያ ክልል ከ5 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች የቤት መስሪያ ቦታ አበረከተ

መጋቢት 3/2013 (ዋልታ) – የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ለ5 ሺህ 794 የፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ግንባር ቀደም አርሶ አደሮች የቤት መስሪያ ቦታ መስጠቱ ተገልጿል፡፡
በቤት መስሪያ ቦታ ርክክብ ስነ ስርዓት ላይ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የክልሉ ም/ፕሬዚዳንትና የከተማ ክላስተር አስተባባር ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ እና ሌሎች ከፍተኛ የክልሉ መንግስት የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከፊንፊኔ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ኮሚዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡