የኦሮሚያ የ2014 የመኸር እርሻ የዘር ሳምንት ተጀመረ

ሰኔ 22/2014 (ዋልታ) የኦሮሚያ ክልል የ2014 የመኸር እርሻ የዘር ሳምንት በምዕራብ ሸዋ ዞን ደንዲ ወረዳ ተጀመረ።

በክልሉ በዘንድሮው የመኸር እርሻ 6 ነጥብ 3 ሚሊየን ሄክታር መሬት ለማረስ እቅድ የተያዘ ሲሆን ከዚህ መካክል 4 ነጥብ 5 ማሊየን ሄክታር መሬት በክላስተር የሚለማ ነው።

በመኸር እርሻው ለስንዴ እርሻ ልዩ ትኩረት የተሰጠው ሲሆን 1 ነጥብ 6 ሚሊየነ ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዷል።

በክልሉ በበጋ ስንዴ ልማት ከሚለማው አንድ ሚሊየን ሄክታር ጋር ተዳምሮ በክልሉ 107 ሚሊየን ኩንታል ስንዴ ሲጠበቅ ይህም ኢትዮጵያ ዜጎቻን መግባ ስንዴን ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የያዘችውን እቅድ ለማሳካት ድርሻው የጎላ ነው ተብሏል፡፡

አሳንቲ ሀሰን (ከምዕራብ ሸዋ)