የከተማ አስተዳደሩ በባሌ ዞን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 78 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የካቲት 11/2014 (ዋልታ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኦሮሚያ ክልል በባሌ ዞን በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች 78 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።

የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በባሌ ዞን በድርቅ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ለማድረግ ባሌ ሮቤ ከተማ መግባታቸው ይታወሳል።