የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ካውንስል ምስረታ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙዔል ኡርቃቶ

ሚያዝያ 15/2013 (ዋልታ) – የኢትዮጵያ ከፍተኛ ትምህርት ጥራት ካውንስል ምስረታ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።

የምስረታ ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙዔል ኡርቃቶ ከዚህ በኋላ የትምህርት አሰጣጥ አገልግሎቱ በአክሪዲቴሽን ሲስተም እንደሚሆን ገልጸዋል።

ካውንስሉ በቀጣይ አስር አመታት በተለያዩ ዘርፎች ምን ያህል የሰለጠነ የሰው ሃይል እናበቃለን የሚል ግብ አስቀምጦ እንደሚሰራም ተናግረዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወልደማሪያም በበኩላቸው፣ ካውንስሉ ለአጠቃላይ የትምህርት ጥራትና አግባብነት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ገልጸዋል።

ትምህርት የሰብአዊ ካፒታል ልማት ማዕከል መሆኑን የጠቆሙት ፕሮፌሰር ሂሩት፣ የትምህርት ጥራት ደግሞ የአንድን ሃገር እድገት አመላካች ባሮ ሜትር ነው ብለዋል።

በመሆኑም ሰዎች ራሳቸውንና አካባቢያቸውን አውቀውና መርምረው ለሰው ልጆች ጥቅም ላይ ማዋል እንዲችሉ ጥራት ያለው ትምህርት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

(በነስረዲን ኑሩ)