የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች “ተከትለንሃል” በሚል ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው

የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች

ኅዳር 18/2014 (ዋልታ) የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና አርቲስቶች “ተከትለንሃል” በሚል መሪ ቃል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)ን በመከተል ወደ ጦር ግንባር እየዘመቱ ነው።

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና የከተማዋ ነዋሪዎች የአገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ወደ ጦር ግንባር ለሚዘምቱ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና አርቲስቶች አሸኛኘት በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

በአሸኛኘት መርሃ ግብሩ ላይ የከተማዋ አስተዳደር አመራሮች፣ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችና አርቲስቶች የአሸኛኘት ሥነ ሥርዓት ላይ መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል።