የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ከመከላከያ ሰራዊት ጎን ለመቆም ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጹ

ሐምሌ 23/2013 (ዋልታ) – የሀገር ህልውናን ለማዳን የተመመውን የመከላከያ ሰራዊት ገን በመቆም በኪነ ጥበብ ሀይል ኢትዮዽያ እንድታሸንፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ገልፀዋል::
የሀገርን ሉአላዊነት ለመድፈር ግብን ሰንቆ የመጣውን የውል ወራሪ ሃይል ግብ ቅዠት ለማድረግ መተኪያ የሌለው ህይወታቸውን ከገበሩ ጀግኖች አባቶች ጎን በመቆም የኪነ-ጥበብ ስራዎች ያበረከቱት አስተዋፅኦ የጎላ መሆኑ ተገልጿል::
ከያኒው ጥበብን ታጥቆ የሀገርን ህልውና ለመታደግ ከዘመተው ከሀገር ደጀን መከላከያ ጎን በመቆም ብርታት እና ጉልበት ሊሆን እንደሚገባም ተገልጿል::
(በሔብሮን ዋልታው)