የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በሁለተኛ ድግሪ ያስተማራቸውን 56 ተማሪዎችን አስመረቀ

የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ በህብረተሰብ ጤና ሳይንስ እና ስነ-ተዋልዶ በሁለተኛ ድግሪ ያስተማራቸውን 56 ተማሪዎችን አስመርቋል።
የካቲት 12 ሆስፒታል ከሚሰጠው የህክምና አገልግሎት ባሻገር በ9 የትምህርት ዘርፎች ከ500 በላይ ተማሪዎችን እያሰለጠነ ይገኛል።
በምረቃ ስነሥርዓቱ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ አለም በአደገኛ ወረርሽኝ በምትፈተንበት ወቅት ከሰለጠናችሁበት የሙያ ዘርፍ ብሎም ካለፋችሁበት የህይወት ተሞክሮ ጋር በማስተሳሰር በሙያቸው ለማህበረሰባቸው ጤንነት እንዲቆሙ ጠይቀዋል።
በቁምነገር አህመድ