የካፋ ባህል ማዕከል በአዲስ አበባ ሊገነባ ነው

ነሃሴ1/2013(ዋልታ) – የቡናን ተክል ጨምር የተለያዩ ባህሎች መገኛ ለሆነችው ካፋ በአዲስ አበባ ባህል ማዕከል ሊገነባ ነው።ለባህል ማዕከሉ ግንባታ የሚሆን የቦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓትም ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ አስተዳደር ካፋን ጨምሮ ለተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች የባሕል ማዕከል መገንቢያ ቦታ እየሰጠ መሆኑ ይታወቃል።

ይህም ከተማዋ ሁሉም ኢትዮጵያውያን በእኩልነት ባህላቸውንና ማንነታቸውን የሚያስተዋዉቁባት መሆኗን ያሳያል ተብሏል።

የቡና ተክልን ጨምሮ የረጅም ዘመን የታሪክና የባህል ባለቤት ለሆነችው የካፋ ዞን በከተማዋ የባህል ማዕከል ሊገነባ መሆኑን ነው ዛሬ የተገለጸው።

በቦታ ርክክብ ሥነ-ሥርዓቱ የከተማዋ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አበቤ፣ የካፋ ዞን የአገር ሽማግሌዎች፤ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

(በሳራ ስዩም)