የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ አዲስ አበባ ገቡ

የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ

ነሐሴ 27/2013 (ዋልታ) የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሯ ራይሸል ኦማሞ ለስራ ጉብኝት አዲስ አበባ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ብርቱካን አያኖ በቦሌ አለማቀፍ አየር ማረፊያ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ደመቀ መኮንን እና ከሌሎች የስራ ኃላፊዎች ጋር ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።