የክላሸንኮቭ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለች

ታኅሣሥ 6/2014 (ዋልታ) በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የክላሸንኮቨ ጥይት ደብቃ የተገኘች ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሏን ፖሊስ አስታወቀ።

የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ያለው ዘለቀ ለኢዜአ እንደገለጹት ግለሰቧ ትናንት ምሽት 3:00 ላይ ነው በቁጥጥር ስር የዋለችው በመኖሪያ ቤቷ ከህብረተሰቡ ጥቆማ የደረሰው ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ የክላሸንኮቭ ጥይት ተከማችቶ በመገኘቱ ነው።

ተጠርጣሪ ግለሰቧ በቁጥጥር ስር ውላ ምርመራ እየተደረገባት መሆኑን ጠቁመዋል።

ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝም ክትትል እየተደረገ መሆኑን ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል።

ሕብረተሰቡ አካባቢውን ከሕገ ወጥ ተግባራትና ሰርጎ ገቦች ለመጠበቅ እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።