የክልሉ ሕዝብ ለመከላከያ ሰራዊት ከ1 ሺሕ 200 በላይ ፍየልና በግ አበረከተ

መስከረም 18/2015 (ዋልታ) የሶማሌ ክልል ሕዝብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት ከ1 ሺሕ 200 በላይ ፍየልና በግ አበረከተ፡፡

ድጋፉ ለ2ኛ ጊዜ ከክልሉ ሕዝብ የተሰበሰበውን የእርድ እንስሳት ድጋፍ የክልሉ የሀገር ሽማግሌዎች በፋፈን ዞን ሸበሌ ወረዳ ተገኝተው ማስረከባቸውን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን መረጃ አመላክቷል፡፡

የክልሉ ሕዝብ የሀገርን ዳር ድንበር ለሚያስከብረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ድጋፍ በማድረግ ደጀንነቱን በተግባር ማሳየቱን የሀገር ሽማግሌዎቹ ተናግረዋል፡፡

የክልሉ ህዝብ ከምንጊዜውም በላይ ለአገር ሉዓላዊነት እየተዋደቀ ለሚገኙት የሀገር መከላከያ ሠራዊት እና ሌሎች የሀገር ባለውለታ የፀጥታ ኃይሎች የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥልም ገልጸዋል።

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW