የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የአስከሬን ሽኝት መርኃግብር እየተካሄደ ነው

ሰኔ 29/2013(ዋልታ) – የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና አስከሬን ከመኖሪያ ቤታቸው ወደ መስቀል አደባባይ ሽኝት እየተደረገለት ይገኛል፡፡

የክብርት ዶክተር አበበች ጎበና የቀብር ስነ-ሥርዓት በዛሬው ዕለት ከቀኑ በ9 ሰዓት በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል።

በመርኃግብሩ መሰረት ከረፋድ 3 ሰዓት ጀምሮ እስከ 5 ሰዓት በመኖሪያ ቤታቸው የአስክሬን ሽኝት መርኃግብር እየተከናወነ ይገኛል፡፡

ከቀኑ 6 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በመስቀል አደባባይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው እና ቤተሰቦቻቸው በሚገኙበት አሸኛኘት እንደሚደረግ ከአበበች ጎበና የህጻናት ክብካቤና ልማት ማህበር ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።