የክተት ጥሪ ተቀብሎ የሰለጠነ የአማራ ልዩ ኃይል ተመረቀ

ጥቅምት 23/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያን ለማዳን የአማራ ክልል መንግስት ያወጀውን የክተት ጥሪ ተቀብሎ የሰለጠነ የአማራ ልዩ ኃይል ዛሬ ተመርቋል።

የአማራ ልዩ ኃይል ከመከላከያ፣ ከሚሊሻና ከፋኖ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለማፍረስ በሚል ከንቱ ቅዠት ተነስቶ አማራንና አፋርን መውረር የጀመረውን የትግራይ ወራሪ ቡድንን ለመቅበር በከፍተኛ ወኔና እልህ ተነስቷል።

በምረቃው ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ/ር)፣ አቶ ላቀ አያሌው እንዲሁም ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራልና የክልል የስራ ኃላፊዎች መገኘታቸውን ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡