የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል 10 ሚሊዮን ክትባት ተሰጥቷል – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ሰኔ 27/2016 (አዲስ ዋልታ) በዘንድሮው ዓመት በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሌራ ወረርሽኝን ለመከላከል 10 ሚሊዮን ክትባት መሰጠቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኩፍኝ ወረርሽኝን ለመከላከልም በ58 ወረዳዎች ክትባት ተሰጥቷል ብለዋል።

የወባ በሽታን ለመከላከል በርካታ አጎበሮች መሰራጨታቸውንም አንስተዋል።

በተለይ የመድሃኒት አቅርቦትን በአገር ውስጥ በመተካት ረገድ ከ8 በመቶ ወደ 36 በመቶ ማደረስ እንደተቻለ ገልጸዋል።

በጤናው ዘርፍ በተሰጠው ትኩረትም በአርባ ምንጭ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ከፍተኛ ሆስፒታል ይመረቃል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በግሉም ዘርፍ የሆስፒታል ግንባታዎች በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ጠቁመዋል።