የኮሚሽኑ ሠራተኞች ለሰራዊቱ ደም ለገሱ

ነሀሴ 12/2013 (ዋልታ) – የፕላንና ልማት ኮሚሽን ከተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ጋር በመሆን ለመከላከያ ሰራዊት ደም ለገሱ፡፡

ሠራተኞቹ ደም በመለገሳቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው የህልውና ዘመቻው እስኪጠናቀቅ ድረስ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መናገራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ የኢፌዴሪ ፕላንና ልማት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ እንዲሁም የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ሰራተኞች የደም ልገሳ አድርገዋል፡፡