‘የኮሚዩኒኬሽን መንገዶቻችን ለምርጫ ሰላምና ደኅንነት’ በሚል ርዕስ የአዲስ ወግ ውይይት እየተካሄደ ነው

 

‘ የኮሙዩኒኬሽን መንገዶቻችን ለምርጫ ሰላምና ደኅንነት’ በሚል ርዕስ አዲስ ወግ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እየተካሄደ ይገኛል።

በስነ አዕምሮ ህክምና ባለሙያው ዶ/ር ምህረት ደበበ አወያይነት፤ ዕዝራ አባተ (ፒኤችዲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስነ ጥበባት ኮሌጅ ዲን፣ ኢ/ር ጌታሁን ሔራሞ የኬሚካል መሐንዲስ እንዲሁም ዶ/ር አጋረደች ጀማነህ፣ መምህርትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመማር ማስተማር ድጋፍ ሰጪ ቢሮ ዳይሬክተር ውይይት እያካሄዱ መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ አመልክቷል።