የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል በዘመቻ ሙያ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ

ሰኔ 30/2014 (ዋልታ) የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል በዘመቻ ሙያ ያሰለጠናቸውን የሰራዊት አባላት አስመረቀ፡፡

በምርቃት ፕሮግራሙ ላይ በመገኘት ለተመራቂዎች የሥራ መመሪያ የሰጡት የኮማንዶና አየር ወለድ ኃይል ሥነልቦና ግንባታ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሎኔል ገዛኸኝ ነጋሽ የዘመቻ ሙያተኛ እራሱን አብቅቶ ሌሎችን በማብቃት ሠራዊቱን ለድል የሚያበቃ እና በግዳጅ ውስጥ ወሳኝ ሚናን የሚጫወት መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ተመራቂዎቹም በዚህ ደረጃ ያለባቸውን ኃላፊነት ተገንዝበው የተጣለባቸውን ሙያዊ ግዴታ በብቃት እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

የኮማንዶና አየር ወለድ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ኮሎኔል ኤፍሬም ዘገዬ በበኩላቸው ስልጠናው በክፍሉ ተደማሪ አቅምን ለመፍጠር ያለመ መሆኑን በመግለፅ ውጤቱ በሚፈለገው ደረጃ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ከተመራቂዎች መካከል መሠረታዊ ወታደር አቤል ታደሰና አለማየሁ ግዛቸው በሰጡት አስተያየት በስልጠና ቆይታቸው በቶፖግራፊ እና አጠቃላይ የዘመቻ ሥራ በቂ እውቀት ማግኘታቸውን ገልጸው በሰለጠኑበት ሙያም በሰንደቅ አላማው ፊት በፈፀሙት ቃለ መሀላ መሠረት ግዳጃቸውን በቁርጠኝነት እንደሚወጡ መናገራቸውን ከመከላከያ ሰራዊት ፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW