ሰኔ 27/2016 (አዲስ ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የኮሪደር ልማት ለመላው ኢትዮጵያዊ ስኬት ነው ሲሉ ገለጹ።
የኮሪደር ልማትን ገና ስናስብ ከ38 ከተማ ከንቲባዎች ጋር እንዴት እንደምንሰራ እና እንዴት እንደምናስብ ተወያይተናል ብለዋል።
የተሰራው ሥራ የከተማዋን ደረጃ ከፍ ያደረገ ጥሩ ጅምር ቢሆንም ነገር ግን ገና ብዙ ሥራ ይጠበቅብናል ሲሉም ገልጸዋል።
ፕሮጀክቱን ወደ ሌሎች ከተሞቻችን እናስፋፋዋለን ነው ያሉት።
ለኮሪደር ልማት የተጠቀምናቸው መብራቶች ስማርት መብራቶች በመሆናቸው ከብርሃን ባሻገር የካሜራ ሲሲቲቪ አላቸው፤ ኔትወርክን ያሳልጣሉ ወደ ፊት ትስስሩ ሲያድግ የትራፊክ መጨናነቅ ያለበትን መረጃ ይሰጣል በማለትም ተናግረዋል።
ከሸራተን ሆቴል እና ሳይንስ ሙዚየም ጀርባ ያለውን ግንባታ ስንሰራ የግንባታ ግብዓቱን ሙሉ በሙሉ ከውጭ አስመጥተን ነበር ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሌሎቹን የኮሪደር ልማት ግንባታ ግን ከቀደመው ሳምፕል በመውሰድ ያከናወነው በራሳችን ኢንዱስትሪዎች በተመረቱ ምርቶች ነው ብለዋል፡፡