የኮሮናቫይረስ ሕግን የጣሱት ፕሬዚደንት ሴባስቲያን 3,500 ዶላር ተቀጡ

የደቡብ አሜሪካዊቷ አገር ቺሊ ፕሬዚደንት ሴባስቲያን ፒኔራ የኮሮናቫይረስ ሕግን በመጣሳቸው 3 ሺህ 500 ዶላር ገንዘብ ተቀጡ።
ፕሬዚደንቱ ቅጣቱ የተጣለባቸው የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ሳያደርጉ ‘ሰልፊ’ በመነሳታቸው ነው።
ሰባስቲያን በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ ይኸው ከአንዲት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ካላደረገች ሴት ጋር የተነሱት ፎቶ በስፋት ከተሰራጨ በኋላ ይቅርታ ጠይቀዋል።
ፕሬዚደንቱ በካቻጓ በሚገኘው ቤታቸው አቅራቢያ ባለ የባህር ዳርቻ ሴትዮዋ አብራቸው ፎቶ እንዲነሱ ስትጠይቃቸው “የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ነበረብኝ” ብለዋል።
ቺሊ ሕዝብ በሚገለገልባቸው ቦታዎች የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግን የሚያዝ ጥብቅ ሕግ አላት  (ምንጭ ፡- ቢቢሲ)