የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ የመከላከሉ ስራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ተገለጸ

መጋቢት 27/2013 (ዋልታ) – የግልና የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል በትኩረት መስራት እንዳለባቸውም የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ አሳስበዋል፡፡

ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ቀጣይ የአገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶች መገኛ እንደመሆናቸው የቫይረሱን ስርጭት በመከላከል በኩል ሀላፊነታቸው ድርብ እንደሆነ አውቀው ተማሪዎችም ሆነ የዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ ሊጠነቀቁ ይገባል ብለዋል፡፡

ከወረርሽኙ በፍጥነት መዛመት ጋር ተያይዞ በሁሉም የመንግስት ተቋማት በጤና ሚኒስቴር በኩል የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከልና ለመቆጣጣር በወጣ መመሪያ ቁጥር 30/2013 ላይ ግንዛቤ በመፍጠርና ለመከላከሉ ስራ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን ማሟላት እንደሚገባቸው ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡