የኮትዲቯሩ ፕሬዝዳንት የኢትዮጵያን መንግሥት ቁርጠኝነት አደነቁ

ታኅሣሥ 8/2014 (ዋልታ) የኮትዲቯሩ ፕሬዝዳንት ኦላሳኔ ኦታራ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) መንግሥት ለአፍሪካ ልማት እያሳየ ያለውን ቁርጠኝነት አደነቁ፡፡

ፕሬዝዳንት ኦላሳኔ ኦታራ በቲውተር ገጻቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ጋር በነበራቸው ውይይት የሁለቱን አገራት ትብብር በማሳደግና በኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ መምከራቸውን ጽፈዋል።

ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ስለሚቻልባቸው መንገዶች እንደተወያዩም ነው ያሳወቁት።