የዋልታ ሠራተኞች የምስጋና ቀንን አከበሩ

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሠራተኞች የምስጋና ቀንን አከበሩ፡፡
የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ዋና ሥራ አስፈጻሚ ንጉሴ መሸሻ (ፒኤችዲ) ባለፉት ጥቂት ዓመታት እንደ ሀገር ፈተና ያጋጠመን ቢሆንም ሳንደነቃቀፍ የኢትዮጵያን አኩሪ የድል ታሪክ መጻፍ የቻልን ትውልድ በመሆናችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል፡፡
ምስጋና በረከትና መትረፍረፍ የሚያመጣ በመሆኑ በማመስገን እና በጽናት በመጓዝ የበለጸገች ሀገርን ለመፍጠር እንሰራለን ነው ያሉት፡፡
ኢትዮጵያ በብዙ ፈተናና ውጣ ውረድ ብትፈተንም በፅናት ተቋቁማ ዛሬ ላይ በመድረሷ የምስጋና መርኃ ግብሩ ተካሂዷል፡፡