የዋልታ ሰራተኞች ከተለያዩ አካባቢ ተፈናቅለው በደሴ ከተማ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች ድጋፍ አደረጉ

መጋቢት 20/2014 (ዋልታ) የዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት ሰራተኞች በጦርነት ለተጎዱ እና ከተለያዩ አካባቢዎች ተፈናቅለው በደሴ ከተማ መጠለያ ውስጥ ለሚገኙ ዜጎች የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የደቡብ ወሎ ዞን አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የቅድመ መከላከል አስተባባሪ መሃመድ ሰይድ አልባሳት አሰባስበው ለላኩት የሚዲያ ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በአሁኑ ሰዓት ለተፈናቃዮች የምግብ፣ የቤት ቁሳቁስ እና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፎች እንደሚያስፈልጉም ገልጸዋል።

በዞኑ የሚገኙ ቢሮዎች በጦርነት ወቅት በመዘረፋቸው የጽሕፈት መሳሪያ እና የቢሮ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍም እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ቢሮ የሚቀይሩ እና የሚያድሱ ተቋማት የቀድሞ መገልገያቸውን ለወደሙ ተቋማት እንዲለግሱም ጥሪ አቅርበዋል።

እንየው ቢሆነኝ (ከደሴ)

 

ለፈጣን መረጃዎች፦

ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW

ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth

ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured

ቲዊተር https://twitter.com/walta_info

አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!