የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ለ“ትንሿ ኢትዮጵያ” ህጋዊ አውቅና ሰጠ

በአሜሪካ ዋሽንግተን ዲሲ ከተማ ውስጥ “ሊትል ኢትዮጵያ” ወይንም “ትንሿ ኢትዮጵያ”  ለሚባለው አካባቢ የተሰጠው ስያሜ ህጋዊ አውቅና ማግኘቱን በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍፁም አረጋ ተጋናግረዋል።

አምባሳደር ፍፁም የዋሽንግተን ዲሲ ከተማ አስተዳደር እና የአሜሪካ የንግድ ማህበረሰብ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” እውቅና እንዲያገኝ ላበረከቱት ድጋፍና አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርበዋል።

በዋሽንግጸን ዲሲ ለ”ትንሿ ኢትዮጵያ” የተሰጠው አውቅና ሁለቱ ሀገራት ያላቸውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ከማሳደጉም በላይ በማህበራዊ እና በባህላዊ ጉዳዮች ወዳጅነታቸውን እደሚያጎለብተው አምባሰደደሩ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ገልጸዋል።