የዋጋ ንረት እና የኢኮኖሚ አሻጥሩን መከላከል ላይ ያለመ ውይይት እየተካሄደ ነው

ነሀሴ 24/2013 (ዋልታ) – የዋጋ ንረት እና የኢኮኖሚ አሻጥሩን መከላከል ላይ ያለመ ውይይት ከባለ ድርሻ አካላት ጋር በመካሄድ ላይ ይገኛል::

ውይይቱ ላይ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ባሰሙት ንግግር  “በስም ነጋዴ በተግባር  አገር አፍራሽ “የሆኑ አካላትን በጋራ እንከላከል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በአሁኑ ወቅት ኢኮኖሚያዊ ምክንያት የሌለበት በአሻጥር የኑሮ ውድነት እንዲከሰት እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

ሚኒስትሩ የንግድ አሻጥር መረብን በመበጣጠስ የኑሮ ውድነት አሳሳቢነት ደረጃን  መቀነስ ይገባል ብለዋል::

በዚህም በትኩረት እስከ መኸር መግቢያ ታህሳስ  ድረስ በጋራ የመስራትን  አስፈላጊነት አብራርተዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር  የዋጋ ንረት እና የኢኮኖሚ አሻጥሩን መከላከል  በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከአስመጪዎች ፣ከሸማቾች መብት ጥበቃ ማህበራት፣ ከአምራቾች እና ከሕብረት ስራ ማህበራት እንዲሁም  ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ነው ውይይቱን እያካሄደ የሚገኘው።