የዋጋ ግሽበት በአራት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ቀነሰ

ሐምሌ 5/2014 (ዋልታ) የሰኔ ወር የዋጋ ግሽበት በአራት ወራት ውስጥ ለመጀመሪያ ቅናሽ ማሳየቱን የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ አስታወቀ፡፡
ከነሐሴ ወር ወዲህ ለታየው የዋጋ ቅናሽ የምግብ ዋጋ ጋብ ማለት አስዋጽኦ ማበርከቱ እና የዋጋ ግሽበቱ በግንቦት ወር ከነበረበት 37 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 34 በመቶ ዝቅ ማለቱን ከኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
የምግብ ዋጋ ግሽበቱ በግንቦት ከነበረበት ከ43 ነጥብ 9 በመቶ ወደ 38 ነጥብ 1 በመቶ ዝቅ ያለ ሲሆን ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦቶች ዋጋ ግሽበት ደግሞ በ28 ነጥብ 4 በመቶ ገደማ መሆኑን መረጃው ያሳያል።
በኢትዮጵያ የሸማቾች ዋጋ ግሽበት ዕድገት ቢያንስ በዘጠኝ ዓመት ተኩል ጊዜ ውስጥ ከፍተኛው ደረጃ ላይ የደረሰ ሲሆን መንግሥት ባለፈው ሳምንት ለነዳጅ ያደርግ የነበረው ድጎማ ለማቆም ማቀዱን በነዳጅ ዋጋ ላይ በአማከይ የ38 በመቶ ጭማሪ መታየቱ የዋጋ ግሽበት የበለጠ ሊጨምር እንደሚችል ያመላክታል፡፡
በጥቅምት 2013 ዓ.ም ትሕነግ በሀገር መከላከያ ሠራዊት ሰሜን እዝ ላይ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ በትግራይ ክልል ጦርነት የተቀሰቀሰ ሲሆን ዝናብ ባልጣለባቸው የሀገሪቷ ክፍሎች ደግሞ ድርቅ አጋጥመሏ፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ሁለቱ ክስተቶች ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና ከአንበጣ ወረራው ጋር ተዳምረው በሀገሪቱ የማምረት አቅም ላይ የሚያሳድሩት አሉታዊ ተጽእኖ ምክንያት የዋጋ ግሽበቱ መባባሱ ይነገራል።
ከላይ ያሉት ሰው ሰራሽና እና የተፈጥሮ አደጋዎች በኢትዮጵያ ላይ ያስከተለት ጉዳት ሳያበቃ የሩሲያ እና የዩክሬይን ጦርነት በዓለም የማዳበሪያ፣ ነደጅ እና የምግብ ዘይት አቅርቦት ላይ ያሰከተለው የዋጋ ግሽበት በኢትዮጵያ ያለው የዋጋ ግሽበት እንዲባባስ የራሱን ድርሻ እንደተጫወተ ይታመናል፡፡
በዚህ ሁላ የወጋ ግሽበት አዙሪት ውስጥ የኢትዮጵያን ብር የመግዛት አቅም ከዓለም አቀፍ መገበያያ ገንዘቦች አንጻር እንዲዳከም መደረጉ የዜጎች የመግዛት አቅም እንዲዳከም አድርጓል፡፡
በሔለን ታደሰ