የውይይት መድረኩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት መፍጠር መቻሉ ተገለጸ

መጋቢት14/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በየደረጃው ሲከናወን በነበረው የሕዝብ ውይይት
ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት መፍጠር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ገለጸ።
በብልጽግና ፓርቲ የመጀመሪያ ጉባኤ የተቀመጡ አቅጣጫዎችና ውሳኔዎች ከኅብረተሰቡ ዘላቂ ፍላጎቶች ጋር የተጣጣሙ እንደሆኑ እና መድረኩ ችግሮችን በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የጋራ መግባባት መፍጠር መቻሉን ፓርቲው አስታውቋል፡፡
በመዲናዋ ከ88 ሺሕ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች የተሳተፉበት የሕዝብ ውይይት መድረክ ተጠናቋል።
ለኢትዮጵያ ብሎም ለአዲስ አበባ ዘላቂ ሰላም፣ እድገትና ብልጽግና ሕዝቡ ራሱ ባለቤት እንደሆነም በተከናወኑ የሕዝብ ውይይት መድረኮች ላይ የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።
በመዲናዋ በ11ዱ ክፍለ ከተሞች 132 ያህል የውይይት መድረኮች የተከናወኑ ሲሆን ከ88 ሺሕ በላይ የኅብረተሰብ ክፍሎች መሳተፋቸውን ከፓርቲው ጽሕፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።