የውጭ ተፅዕኖን ለመቋቋም ራስን በምጣኔሃብት መቻል ወሳኝ ነው- ም/ጠ/ሚ ደመቀ መኮንን

ጥቅምት 6/2014 (ዋልታ) የውጪ ተፅዕኖን ለመቋቋም ግብርናን በማዘመን በምጣኔሃብት ራሳችንን መቻል ወሳኝ ነው ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ተናገሩ፡፡
በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በኦሮሚያ ክልል የግብርና ሥራዎችን እየጎበኘ ነው።
ግብርናን ለማዘመን በኦሮሚያ ክልል የተሰራውን ሥራ እንደ አገር በማስፋፋት ታሪክ መስራት ይቻላል ብለዋል፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚመሩት የሚኒስትሮች ልዑክ በምስራቅ ሸዋ ዞን አዳሚ ቱሉ ጂዶ ኮምቦልቻ ወረዳ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ እና የበቆሎ ማሳን መጎብኘቱን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡
ልዑኩ ረፋድ ላይ በምስራቅ ሸዋ ዞን አደኣ ወረዳ በኩታ ገጠም የለሙ ሰብሎች፣ አትክልት እና ፍራፍሬዎችን መጎብኘቱን መዘገባችን ይታወሳል።
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት፦
የአማርኛ ፌስቡክ ገፃችንን ይወዳጁ ይከተሉ
ከአረብኛ ፌስቡክ ገፃችን ጋርም ይጓዙ
የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
የትዊተር ገፃችንን ይከተሉ