የውጭ ኃይሎች በኢትዮጵያ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት እንቃወማለን – የጎባ ከተማ ነዋሪዎች

ጥቅምት 27/2014 (ዋልታ) የውጭ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነትና ጫና አጥብቀው እንደሚቃወሙ በባሌ ዞን የጎባ ከተማና አካባቢዋ ነዋሪዎች አስታወቁ።

ነዋሪዎቹ የሀገር መከላከያ ሰራዊትን የሚደግፍና የውጭ ኃይሎች ጫናን የሚያወግዝ ሰልፍ ዛሬ በጎባ ከተማ አካሂደዋል።

አሸባሪው የሕወሓት ቡድን የጥፋት ሴራ በማክሸፍ የሀገር ህልውናን ለማስከበር አስፈላጊውን መስዋዕትነት እንደሚከፍሉም አስታውቀዋል፡፡

“መከላከያችን የሉዓላዊነታችን ዓርማ ነው፣ ሉዓላዊነታችንን በደምና አጥንታችን እናስከብራለን፣ አሸባሪዎቹ ሕወሓትና ሸኔ የኢትዮጵያዊያን ጠላት ናቸው” ሲሉም ነዋሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት አውግዘዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የከተማዋ ነዋሪዎች የውጭ ኃይሎች ጣልቃ ገብነትን በመቃወም ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡም ጠይቀዋል፡፡