ሐምሌ 01/2014 (ዋልታ) የኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ በመገደላቸው የተሰማውን ሀዘን ገለጸ፡፡
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጃፓኑ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሺንዞ አቤ አሳዛኝ አሟሟት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ገልጾ ለህልፈተ ህይወታቸው ምክንያት የሆነውን አሳዛኝ ድርጊት በጽኑ አውግዟል።
ሽንዞ አቤ የኢትዮጵያ መልካም ወዳጅ እንደነበሩ ያተተው መግለጫው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በኢትዮጵያና ጃፓን መካከል ያለውን ታሪካዊ ግኑኝነት ወደ ተሻለ ደረጃ በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ ሚና መጫውታቸውን ጠቅሷል።
የአፍሪካ -ጃፓን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር በማድረግ የቶኪዮ ዓለም አቀፍ የአፍሪካ ልማት መድረክ (ቲካድ)ን በማጠናከርም ሽንዞ አቤ የጎላ ሚና የተጫወቱ መሪ እንደነበሩ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በዘሀን መግለጫው አውስቷል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒስትር ላይ በተፈመው ግድያ አውግዞ ለወዳጅ የጃፓን ሕዝብ፣ ለጃፓን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እና ለሟች ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኛቷል።
የቀድሞ የጃፓን ጠቅላይ ሚኒትር ሺንዞ አቤ በጥይት ተመተው የተገደሉት በደቡባዊ ጃፓን በምትገኝ ናራ ተብላ በምትጠራ ከተማ ጎዳና ላይ የፖለቲካ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ሳሉ ከጀርባቸው በተተኮሰ ጥይት ተመተው መሆኑ ታውቋል።