የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በሑመራ እየተካሄደ ነው

ሰኔ 02/2013 (ዋልታ) – በአሸባሪው ህወሓት ሲደርስባቸው የነበሩ ግፎችንና የውጭ ጣልቃ ገብነትን የሚያወግዝ ሠልፍ በሑመራ እየተካሄደ ይገኛል።

ሰልፈኞቹ በአሸባሪው ህወሓት አገዛዝ ዘመን የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ በደሎች ደርሰውበታል፣  በርካቶች ለህልፈት ተዳርገዋል፣ ከሚኖሩበት ተፈናቅለዋል፣ አካላቸው ጎድሏል ብለዋል።

የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ሕዝብ አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች ኃይሎች የሚያነሱት ሐሳብ ያገኘነውን ነጻነት በመንጠቅ ወደ ዳግም ጭቆና ለመመለስ የተደረገ ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡

አሜሪካ በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ መግባቷንም ሰልፈኞቹ ማውገዛቸውን ከአሚኮ ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡