የውጭ ጫናው ኢትዮጵያ ጠንካራ ከሆነች አፍሪካም ትጠነክራለች ከሚል ስጋት የመነጨ ነው – አቶ አባዱላ ገመዳ

አባዱላ ገመዳ

ኅዳር 6/2014 (ዋልታ) ኢትዮጵያ ላይ እየመጣ ያለው የውጭ ጫና ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ጠንክራ ከወጣች አፍሪካም ትጠነክራለች ከሚል ስጋት የመነጨ መሆኑን አንጋፋው ፖለቲከኛ አባዱላ ገመዳ ገለጹ፡፡

ኢትዮጵያ ላይ የውጭ ጫና እየበረታ የመጣው መንግሥት በሁሉም መንገድ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብርና የሕዝብን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ እንደማይሰጥ እና የትኛውንም የእጅ ጥምዘዛ እንደማይቀበል በመግለጹ እንደሆነም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ሉዓላዊነቷን አስጠብቃ ጠንክራ ከወጣች አፍሪካም ትጠነክራለች የሚል ስጋት ስላላቸው ጫና ለማሳደር እየተረባረቡ ነው ማለታቸውን ኢፕድ ዘግቧል፡፡

እንደ ፖለቲከኛው ገለጻ ያለፉት መንግሥታትም ዓባይን የማልማት ፍላጎቱ ቢኖራቸውም አቅም ስላልነበረንና የትኛውም አገር ብድር እንዳያበድርና እንዳይደግፍ በመደረጉ በእኛ ውሃ ሌሎች እየተጠቀሙ ኢትዮጵያውያን ያለንን የተፈጥሮ ሀብት ሳንጠቀም በድህነትና በጨለማ ውስጥ እንድንኖር ተደርጓል፡፡