የዓለም ዐቀፉ የፋይናንስ ተቋም ቅድሚያ ለተሰጣቸው የኢንቨስትመንት ዘርፎች ድጋፍ አደርጋለው አለ

ጥር 20/2014 (ዋልታ) የዓለም ዐቀፉ የፋይናንስ ተቋም በመንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት በተቋሙ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ቼክ ኦማር ሲላ ገለጹ።
ዳይሬክተሩ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የሥራ ኃላፊዎች ጋር የተወያዩ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ በመንግሥት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል፡፡
በውይይታቸውም አሁን እየታየ ያለውን በኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን፣ በንግዱ ከባቢና በተቋማዊ አቅም ግንባታ ዘርፉ የቅንጅት ሥራ በጋራ አጠናክሮ ለመቀጠል ከስምምነት መድረሳቸውን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።