የዓለም የሰነ-ህዝብ ቀን እየተከበረ ነው

ነሀሴ 21/ 2013 (ዋልታ) – የዓለም የስነ-ህዝብ ቀን እየተከበረ ነው::
 
የሁሉም ሰዎችን የስነ-ተዋልዶ ጤና እና መብቶች ማስቀደም የመፍትሔ መንገድ ነው ተብሏል።
 
የህዝብ ቁጥር መጨመር ድህነት የተፈጥሮ ሚዛን መዛባት የጤና ስርዓት ብቁ አለመሆን እንዲሁም የኮቪድ ወረርሽኝ የዓለም ስጋት ስለመሆናቸው ተገልጿል ::
 
ፒኤች እና ኮራ ኢትዮጵያ ባለድርሻ አካላትን በማሰባሰብ በሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ የሰነ-ህዝብ ቀን አብይ ጉዳይ ላይ ተወያይተዋል::
 
የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደስ የህዝብ ቁጥር መጨመር በጤና አገልግሎት ሥራ ተደራሽን በሥራ ዕድል ፈጠራ በሀገር ምጣኔ ዕድገት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩን በመግለፅ በተለይም በአሁን ስዓት የኮቪድ 19 ወረርሽኝን የመከላከል ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል።
 
የዓለም ስነ ህዝብ ቀን በዓለማችን ለ34ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ28ኛ ጊዜ ተከብሯል።
 
(በአክሊሉ ሲራጅ)