የዓለም የወባ ቀን በኦሮሚያ ክልል እየተከበረ ነው

የዓለም የወባ ቀን

ሚያዝያ 21/2014 (ዋልታ) የዓለም የወባ ቀን በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ እየተከበረ ነው።

በሀገር ዐቀፍ ደረጃ ለ15ኛ ጊዜ የሚከበረው የወባ ቀን በአዳማ አበበ ብቂላ ስታዲየም የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በተሳተፉበት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙት እየተከበረ ነው።

ፍትሓዊና ጠንካራ የጤና ሥርዓትን በማጎልበት ወባን እናጥፋ በሚል መሪ ቃል ነው የዘንድሮው የወባ ቀን እየተከበረ የሚገኘው።

በኦሮሚያ ክልል በ3 ዞኖች ላይ ወባን የማጥፋት የሙከራ ትግበራ በመስራት ውጤታማ ሥራ የተሰራ በመሆኑ በክልሉ 13 ዞኖች ላይ ወባን የማጥፋት ተግባር እየተከናወነ ነው ተብሏል።

በ2013 ዓ.ም በኦሮሚያ ክልል አንድም ሰው በወባ በሽታ እንዳልሞተ የተነገረ ሲሆን በተያዘው በጀት ዓመት የ9 ወራት የሥራ እንቅስቃሴ የወባ በሽታ ጫናን ከባለፈው ዓመት ጋር ሲተያይ 20 በመቶ መቀነስ እንደተቻለ ነው የተገለፀው።

እንመርመር እንታከም ወባን እናስወግድ በሚል ወባን የማጥፋት ንቅናቄ ማድረግም ተጀምሯል።

ምንይሉ ደስይበለው (ከአዳማ)

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW