የዛምቢያ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት አረፉ

ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳ

ሰኔ 11/2013 (ዋልታ)  – የዛምቢያ የመጀመሪያው ፕሬዝዳንት ኬኔት ካውንዳ በ97 ዓመታቸው ህይወታቸው አለፈ፡፡

ኬኔት ካውንዳ  ቅኝ ገዥነትን ከሚያወግዙ፣ ከታገሉ እና የነፃነት እንቅስቃሴ ካስጀመሩ የአፍሪካ መሪዎች  መካከል አንዱ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በሳንባ ምች በሽታ በመታመማቸው በዛምቢያ ዋና ከተማ ሉሳካ ውስጥ ሲረዱ ቆይተው ህይወታቸው ማለፉን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡