የየም ልዩ ወረዳ ወጣቶች ሀገር የማፈራረስ ሴራ ለማክሸፍ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ

ነሃሴ 18/2013 (ዋልታ) – የየም ልዩ ወረዳ ወጣቶች በኢትዮጵያ ላይ ከውጭና ከውስጥ የተቃጣውን ሀገር የማፈራረስ ሴራ ከንቱ ለማድረግና ሀገር ለማዳን ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ዝግጁ መሆናቸውን ገለጹ፡፡

ዛሬ በልዩ ወረዳው ሳጃ ከተማ አስተዳደር የልዩ ወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ ነባራዊ ጉዳዮች ዙርያ ከልዩ ወረዳው ሳጃ ክላስተር የተውጣጡ ወጣቶች ጋር የጋራ የውይይት መድረክ አካሂዷል፡፡

መድረኩን አስመልክቶ የልዩ ወረዳው ሴቶች ህጻናትና ወጣቶች ጽህት ቤት ሀላፊ ታሪኳ ጃላ ተሳታፊ ወጣቶችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ከተጀመረው ሀገራዊ ልማት ጎን ለጎን የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ ወጣቶች ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ለሀገር ሰላም ዘብ ልንቆም ይገባል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይም የልዩ ወረዳው ብልጽግና ፓርቲ ጽህት ቤት ሀላፊ ተስፋዬ አሰፋ በበኩላቸው የልዩ ወረዳው ወጣቶች ከዚህ ቀደም ከመንግሥት ጎን በመቆም ሰፊ ስራዎችን የሰሩ መሆናቸውን አስታውሰው አሁን ላይ ኢትየኢትዮጵያን ለመታደግ ወጣቱ በተባበረ ክንድ ሊቆም ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በዋናነት የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እየተዋደቁ ለሚገኙ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አስፈለጊውን ድጋፍ ለማድረግና በተባበረ ክንድ ኢትዮጵያን ለማዳን ያለመ ነው ተብሏል፡፡

ተሳታፊ ወጣቶች ከውይይት መድረኩ መነሻ በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት እኛ ወጣቶች እያለን ኢትየኢትዮጵያ አትፈርስም አቅማችን በፈቀደው ልክ ለሀገራችን ለመስራት ዝግጁ ነን ሲሉ መደመጣቸውን ከየም ልዩ ወረዳ የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል፡፡