የየካ ከፍለ ከተማ የአቅመ ደካማ ቤቶችን የማደስ መርኃ ግብር አስጀመረ

ግንቦት 9/2014 (ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍል ከተማ አስተዳደር የአቅመ ደካማ ወገኖችን ቤት እድሳት ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እያካሄደ ይገኛል።

በክፍለ ከተማው ከ300 በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶችን በሦስት ወራት ለማደስ መታቀዱን ያስረዱት የክፍል ከተማው ዋና ሥራ አስፈጻሚ መራጊያው ተበጀ ከዚህ በፊት ከ600 በላይ ቤቶች ታድሰው ለአቅመ ደካማ ዜጎች መሰጠታቸውን ተናግረዋል።

ክፍለ ከተማው የመዲናዋን ገፅታ ውብ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስፈጻሚው የሕዝብ ጥያቄ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት እየተሰራ መሆኑንም ጠቁመዋል።

በማስጀመሪያ መርኃ ግብሩ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ጥራቱ በየነ እና የየካ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈፃሚን ጨምሮ ባለሃብቶችና በጎ ፍቃደኞች ተገኝተዋል።

በእመቤት ንጉሴ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!