የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ታሪክና ወጎችን የሚዳስስ “ንስር እና ምስር” የተሰኘ መፅሐፍ ተመረቀ

“ንስር እና ምስር” መፅሐፍ

ግንቦት 13/2014 (ዋልታ) በቴዎድሮስ መብራቱ ተፅፎ ለንባብ የበቃው “ንስር እና ምስር” የተሰኘው መፅሐፍ የተለያዩ እንግዶች በተገኙበት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ።

መፅሐፉ የዩኒቨርሲቲ ቆይታ ታሪክ እና ወጎችን የሚዳስስ ነው ተብሏል።

መፅሐፉ በኢትዮጵያ ታላላቅ ዩኒቨርሲቲዎች የሚያስተምሩ፣ የሚማሩ፣ የሚሰሩ እንዲሁም ራሱን የትምህረት ሥርዓት ጭምር የሚያሳይ ነው ተብሏል።

የመካነ አዕምሮ እና የመካ’ን አዕምሮ ወጎች የሚሉ ወጎችን ያካተተ መፅሐፍ እንደሆነም ነው የመፅሐፋ ደራሲ ቴዎድሮስ መብራቱ የተናገረው።

በመፅሐፉም የሀገር ወጎች፣ ማኅበራዊ ህይወትን የሚዳስሱ፣ ወጣትነትን የሚያሳዩ ወጎች እንዳተካተተም ተነግሯል።

መፅሐፉ የዚህን ዘመን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ማኅበራዊ ኑሮ አካዳሚያዊ እና ፖለቲካዊ ግንዛቤን በመዳሰስ የቀድሞዎቹ ከራሳቸው ዘመን ጋር እንዲመዝኑበት፣ መጪዎቹ እንዲመዝኑበት መሆኑ ተገልጿል።

በእመቤት ንጉሤ

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https://bit.ly/3Ma7QTW