ነሃሴ 18/2013 (ዋልታ) – የደሴ ከተማ ነጋዴዎች ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው በጊዜአዊ መጠለያ ጣቢያዎች ለሚገኙ ወገኖች ማዕድ አጋሩ፡፡
መንግሥት እና ኅብረተሰቡ ለተፈናቃዮቹ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለማዳረስ በመረባረብ ላይ ሲሆኑ የደሴ ከተማ አስተዳደር ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃይ ወገኖች ከ100ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጭ መዕድ አጋርቷል፡፡
ደሴ ከተማ ሼል ተብሎ የሚታወቀው አካባቢ የሚሠሩ ነጋዴዎች ወጭዉን በመሸፈን ነዉ ዝግጁቱን ያካሄዱት፡፡
በማዕድ ማጋራቱ ከ2 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች ተሳታፊ መሆናቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡