ኅዳር 15/2014 (ዋልታ) 11ኛ ክልል ሆኖ የተመሰረተው የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጥቷል፡፡
በዚህም
- አቶ ማስረሻ በላቸው ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አልማው ዘዉዴ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪና የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ፋጂዮ ሳፒ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የመሠረተ ልማት ክላስተር አስተባባሪና የትራንስፖርትና መንገድ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አንድነት አሸናፊ – የሠላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
- ወ/ሮ ወሰነች ቶማስ – የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ተክሌ በዛብህ – የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
- ወ/ሮ ገነት መኩሪያ – የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ኢብራሂም ተማም – የጤና ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ተመስገን ከበደ – የንግድና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ
- አሥራት ገ/ማርያም (ዶ/ር) – የደንና አካባቢ ጥበቃ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ፋንታሁን ብላቴ – የባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
- ኢ/ር በየነ በላቸው – የውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አሰፋ ጊንዶ – የአርብቶ አደርና ቆላማ አካባቢ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
- ወ/ሮ ህይወት አሰግድ- የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
- ኢ/ር የማታለም ቸኮለ – የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ተስፋዬ እንዳሻው- የክህሎትና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ ግዛው ጋግያብ – የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
- አቶ የሺዋስ አለሙ – የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ
- አቶ አስራት ሀዳሮ – ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሠው ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ
- ወ/ሪት ቤተልሔም ዳንኤል – የኢንተርፕራይዝና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ ሆነው የተሸሙ ሲሆን ተሿሚዎቹም ቃለ መሀላ መፈጸማቸውን ከካፋ ዞን መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
በተመሳሳይም አቶ ቆጭቶ ገ/ማርያም የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዞቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ሲሾሙ አቶ ጥላሁን ታደመ ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን ተሹመዋል።
አቶ አስራት አበበ ደግሞ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዞቦች ክልል ዋና ኦዲተር ጀነራል በመሆን መሾማቸው ታውቋል፡፡